Coming soon!

This language is currently in review and will be available soon!

ፕሮጀክቱ

ፕሮጀክት ድልድል፡ በሃማኖታዊ ማኅበረሰብ ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል የሃይማኖት ትምህርትን፣ ጾታና ዕድገትን እና የማኅበረሰብ ጤናን ማሰናሰል፡፡

ድልድል በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ዩናይትድ ኪንግደም ሃይኖታዊ ባሕላዊ ጉዳዮች ተጽእኖ የሚያደርጉባቸው የቤት ውስጥ ጥቃቶችን የመቀነስ ዘዴን ማበልጸግ እና ማጠናከር ላይ የሚያተኩር የጥናታዊ ምርምር እና የፈጠራ ፕሮጀክት ነው፡፡ ድልድል የሚለው የትግርኛ ቃል ትርጉሙ ድልድይ ማለት ሲሆን ፕሮጀክቱ በአማኝ ማኅበረሰቦች ዘንድ የቤት ውስጥ ጥቃትን ከመከላከል አንጻር አንጸባራቂ፣ ቅኝ ያልተገዛ እና የተዋሐደ መንገድን በመጠቀም የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን፣ ዘርፎችን እና ባለድርሻ አካላትን ለማሰናሰል የያዘውን ዓላማ የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ፕሮደክቱ ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦች፣ ነገረ መለኮት እና ካህናት የቤት ውስጥ ጥቃትን ከመከላከል አንጻር ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ የሚያሳዩ እና መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት ስለ የቤት ውስጥ ጥቃት ሃይማኖታዊ ባሕላዊ መለኪያዎችን ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ያተኮሩ አዳዲስ ጥናቶችን እና ማስረጃዎችን ማስገኘት ሲሆን አጠቃላይ ዓላማውም በጥሩ ሁኔታ የተሰባጠረ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል ዘዴን መገንባት ነው፡፡

ፕሮጀክት ድልድል በባለ ድርሻ አካላት እና በሚመለከታቸው አካላት መካከል ትብብር እንዲኖር በማስተባበር እና በባሕሎች መካከል በደቡብ-ሰሜናዊ የእውቀት ሽግግር መንገድ የእርስ በእርስ መማማሮች እንዲኖሩ በማበረታታት ተጽእኖውን ከግብ ለማድረስ ያልማል፡፡ በተለይም በቤት ውስጥ ጥቃትና ጾታ ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ላይ በሚሠሩ ምርምሮችና ትግበራዎች ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የንድፈ ዐሳብ መርሖችን በማዘጋጀት እና ትግበራዎችን በመወሰን የምዕራቡ ዓለም ማኅበረሰብ ያለውን ታሪካዊ የበላይነት ለመቀየር ከፍ ያለ ፍላጎት አለን፡፡      

ፕሮጀክቱ የሚዘጋጀው በለንደን በሚገኘው የ SOAS ዩኒቨርሲቲ የታሪክ፣ ሃይማኖት እና ፍልስፍና ትምህርት ቤት ሲሆን የሚመራውም በ UKRI የወደፊት መሪዎች አባሏ በዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ሀገራት ያሉ በርካታ ተሳታፊዎችን፣ አጋሮችን እና የቡድን አባላትን በተጨማሪም የአክሱም ዩኒቨርሲቲን (አክሱም ኢትዮጵያ)፣ የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የነገረ መለኮት ኮሌጅን (መቀሌ ኢትዮጵያ)፣ የኢትዮጵያ ሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርን (አዲስ አበባ ኢትዮጵያ)፣ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየልማትና ክርስቲያኒያዊ ተራድኦ ኮሚሽን (አዲስ አበባ ኢትዮጵያ)፣ Diversity Resource International (ብራይተን ዩናይትድ ኪንግደም)፣ የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲን (ብሪስቶል ዩናይትድ ኪንግደም) እና የሼፊልድ ዩኒቨርሲቲን (ሼፊልድ ዩናይትድ ኪንግደም) አሳትፏል፡፡ ለአራት ዓመት ያህል ፕሮጀክቱ ወጪው ይሸፈን የነበረው በ UK Research and Innovation (Grant Ref: MR/T043350/1) ተቋም ሲሆን በተጨማሪ ፈንድ በ Harry Frank Guggenheim Foundation (Distinguished Scholars Award 2019) ይታገዛል፡፡

ይህ ፕሮጀክት በማኅበረሰቡ ዐሳባዊ ዕውቀት እና የሕይወት ልምድ ላይ በመመሥረት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ማኅበረሰቦች ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ጥናትን እና ተግባርን ከቅኝ ከተገዛ አስተሳሰብ ለማውጣት ካለ ቆራጥነት የመነጨ ነው፡፡ በታሪክ የማኅበረሰብ ጤና፣ ጾታ እና ዕድገት አቀራረቦች ሃይማታዊ አስተሳሰቦችን እና እምነታዊ መሠረት ያላቸው የዓለም አተያዮችን ዘንግተዋቸዋል ወይም ለብቻ መዝነዋቸዋል ወይም በውስን መስተጋብር ቀርበዋቸዋል፡፡ ለዘር እና ጎሳ ጉዳዮች የሚሰጠው ትኩረት እየጨመረ ሲመጣ በርካታ እንቅስቃሴዎች የእምነት ጉዳዮችን ማካተት ጀምረዋል፡፡ አሁን ላይ ያሉ አቀራረቦች አሁንም ቢሆን ከሃይማታዊ ባሕላዊ የዓለም አተያይ ጋር እና ከጉዳይ ተኮር አረዳድ ጋር ያላቸው መስተጋብር አነስተኛ ሲሆን እነዚህ ከአጠቃላይ ታሪክ ጋር፣ ጾታዊ ልማዶች ጋር እና ግለሰባዊ ሥነልቦና ጋር እንዴት እንደሚሰባጠሩ እና በሃይማኖታዊ ባሕላዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ለጾታዊ ጥቃት የሚኖሩ አመለካከቶች እና ምላሾች ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ ከመረዳት አንጻር ችግች አሉ፡፡ በተጨማሪም የምዕራባዊው ማኅበረሰብ ከዓለማዊነት ጋር ያለውን ልምምድ የሚያንጸባርቀው ምዕራባዊ የሆነው ሃይማኖትን የመረዳት መንገድ ልዩ የሆነውን ሀገረኛውን ሃይማኖታዊ ልምድ በቋሚነት ይሸፍነዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማኅበረሰቦች ዘንድ የተሠሩ የማኅበረሰባዊ ባሕል ምርምሮች ላይ የተመሠረተ ሲሆን የምርምሮቹን ውጤቶችም ከግምት ያስገባ ነው፡፡ የታገዘውም በሰሜናዊ የትግራይ ክፍል በገጠር እና በከተማ ማኅበረሰብ ዘንድ ካህናቱ እና ምእመናን የቤት ውስጥ ጥቃትን በሚረዱበት እና በሚያስተናግዱበት ጊዜ ሃይማታዊ ቋንቋ ያለውን የበላይነት ባሳዩ እና በተጨማሪም ስለ ጋብቻ በማስተማር ጊዜ እና በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ግጭቶችን እና ጥቃቶችን በማስታረቅ ጊዜ ካህናት ያላቸውን ወሳኝ ሚና ባሳዩ ግኝቶች ነው፡፡ ምንም ስንኳ አንዳንድ ካህናት ውስብስብ የሆነውን የተጎጂዎችን ወይም የጥቃት ፈጻሚዎችን ሥነልቦና እና የሚኖረውን ከባድ አደጋ በመረዳት ውስጥ ሆነው ምላሽ ለመስጠት ዝግጁነት የጎደላቸው ቢመስሉም ሌሎች ካህናት ግን ከትዳር ውስጥ ጥቃት ጋር የተያያዙ አስቸጋሪ የሆኑ ጸባዮችን ሊቀለብሱ በሚችሉ መንገዶች ነገረ መለኮታዊ ቋንቋዎችን በአግባቡ ይጠቀማሉ፡፡ (የዚህ ጥናት ዘገባ በሚከተለው ማስፈንጠርያ ይገኛል YouTube channel of Cambridge Centre for Christianity Worldwide)

ፕሮጀክቱ ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦች፣ ነገረ መለኮት እና ካህናት ይሄን ነገር ለመከላከል እንዴት ሊያገለግሉ እንደሚችሉ አሳማኝ የሆኑ ማስረጃዎችን በማቅረብ ጭምር የሚደረጉ ጥናቶችን የሚያካትት ሲሆን በተጨማሪም እምነት  በተጠቂዎች ወይም ከጥቃት ተራፊዎች እና ጥቃት ፈጻሚዎች ጸባይ ላይ ያለውን ተጽእኖ እና ለተጠቂዎች ወይም ተራፊዎች ሥነልቦናዊ ማኅበራዊ ድጋፍ ለማድረግ እና ፈጻሚዎችን ለማከም ያለውን እምቅ አቅም ማሳየትን ያካትታል፡፡ ፕሮግራሙ በመላው ሀገሪቷ ያሉ ካህናት ነገረ መለኮትን የመረዳት አቅማቸውን በማሻሻል የጋብቻ እና የቤት ውስጥ ጥቃት ጉዳዮችን በራስ መተማመን ያስተናግዱ ዘንድ እና ተጠቂዎችን እና ጥቃት ፈጻሚዎችን አደጋን በሚቀንስ መንገድ ማገዝ ይችሉ ዘንድ ጥናትን ከአሳታፊ እንቅስቃሴዎች ጋር ማለትም ውይይትን መሠረት ካደረጉ ዎርክሾፖች ጋር ያዋሕዳል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዓላማ የቤት ውስጥ ጥቃትን በተመለከተ ማጣቀሻ ዘዴን ለማዘጋጀት በሚደረገው ጥረት ላይ ይበልጥ ካህናትን አሳታፊ የሆነ አቀራረብን ለማጠናከር መንግሥት መር እና ኢ-መንግሥታዊ የሆኑ በጥቃት ላይ የሚሠሩ የኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላትን እና ሃይማኖታዊ መሪዎችን ወደ አንድ ማምጣት ነው፡፡

በኢትዮጵያ የጥናት፣ የተሳትፎ እና የእውቀት ሽግግር እንቅስቃሴዎች የተቀረጹት በዋነኝነት የኤርትራንና የኢትዮጵያን ስደተኞች እና ጥገኞች ጨምሮ የተለያየ ጎሳ የሃይማኖት ቡድኖችን ለመድረስ በተደጋጋሚ የሚጠራው በዩናይትድ ኪንግደም የቤት ውስጥ ጥቃት ዘርፍ የሃይማኖታዊ ባሕላዊ ጉዳዮች ያላቸውን አንገብጋቢነት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ለመጠቆም ነው፡፡ ስደተኛ ወይም ጥገኛ ማኅበረሰቦች በቤት ውስጥ ጥቃት እጅግ የሚጠቁ እንደሆኑ ነገር ግን ፍላጎታቸው በዋናው የቤት ውስጥ ጥቃት ዘርፍ እንደማይሟላ የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለውን የሃይኖታዊ ባሕላዊ አንገብጋቢነት ደረጃ እና በዘርፉ ላይ ያለውን የብቃት ደረጃ ለመገምገም፣ ሃይማኖታዊ ባለድርሻ አካላት በውጤታማ መንገድ ካለው ነባራዊ መርህ እና የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል አገልግት ጋር እንዴት መዋሐድ እንደሚችሉ ለመረዳት እና በዋነኝነትም ለሃይማኖታዊ ባሕላዊ ልዩ ልዩ አነስተኛ ጎሳዎች፣ ለስደተኞች እና ለጥገኛ ቡድኖች አገልግሎትን ለማሻሻል ጥልቅ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በዩናይትድ ኪንግደም ያካትታል፡፡

ፕሮጀክቱ ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ዕድገት ተኮር ጥናትና ትግበራ ላይ ታሪካዊ ስብጥሮችን በጥልቀት ለማሻሻል እና ከሰሜናዊው ማኅበረሰብ ወደ ደቡባዊ አቻው የማይጠቅሙና የተዋረድ የእውቀት ሽግግር መንገዶችን ለማቃናት፣ ሀገረኛው ሁኔታ ላይ ባተኮሩ ጥናቶች እና ዐሳብን ለማንጸባረቅ እና በውይይት በመተባበር አቀራረብ በተጽእኖ የተቃኙ ተሳትፎዎችን ለማበልጸግ ያልማል፡፡ እነዚህ መርሆች ፕሮጀክቱ ሊያገለግለን የሚያልመውን የድልድዩን መሠረት ይይዛሉ፡፡

ዋናው ዕቅዳችን በትምህርት መስኮች፣ በቡድኖች እና በቤት ውስጥ ጥቃት ጥናት እና ትግበራ ንድፈ ዐሳቦች መካከል ዕውቀትን በመጋራት እንቅስቃሴ ረገድ ድልድይ መሆንና አዲስ መስተጋብርን መፍጠር ነው፡፡ በዋነኝነት በሚከተሉት መንገዶች የፕሮጀክቱን ዕቅድ ለማሳካት እናልማለን፡

ሀ. ከአጋሮች፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከማኅበረሰቡ ጋር በውይይት መንገድ መሥራት እና ሕዝብ ተኮር የጥናት መንገዶችን እና ተግባራትን ተግባራዊ ማድረግ፣

ለ. ጉዳይ ተኮር ዕውቀት ላይ መሥራት እና አዲስ ጥልቅ ማስረጃን ማዘጋጀት

ሐ. ውሕደትን ለማሳካት እና በአንድ ጉዳይ ሁለት እንቅስቃሴ መኖርን ለመከላከል ከነባር የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል ቅርጽ እና መነሣሣቶች ጋር መተባበር፣

መ. በዕውቀት ሽግግር እንቅስቃሴዎች እና በሕዝባዊ ተሳትፎ ትምህርትን፣ አጋርነትን እና ግንዛቤን ማሳለጥ፡፡

ፕሮጀክቱ በርካታ ውጤትችን እንደሚያስገኝ ይጠበቃል፤ ውጤቶቹም፡

ሀ. በሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለ የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል ሃይማኖታዊ ጥናቶችን፣ ዕድገትን እና የሕዝብ ጤናን ድልድይ በመሆን የሚያገናኝ አዲስ አሠራር፣

ለ. ለነገረ መለኮት ተማሪዎች እና ለካህናት በብዙ ቋንቋዎች የሚሰጡ የሥልጠና ሥርዓቶችን፣ ለቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል አገልግሎት ሰጪዎች እና በቤት ውስጥ ጥቃት ጥናት ዙሪያ ለሚሠሩ አጥኚዎች የሚሆን ልዩ ሥርዓተ ትምህርት፣ 

ሐ. በአማኝ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚኖር የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል የተቀናጀ አቀራረብን ከማካተት አንጻር አዲስ የብዙ ባለድርሻ አካላት የዕውቀት ሽግግር መድረክ፣

መ. ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ቋንቋዎችን የሚያዳብር ለጥቃት ፈጻሚዎችና ለጥቃት ሰለባዎች ድጋፍ ለሙከራ የተዘጋጀ ፕሮግራም

ፕሮጀክቱ ተጽእኖ መር ሲሆን ለባለድርሻ አካላት ቡድን፣ ለፕሮጀክቱ ቡድን አባላት እና በቤት ውስጥ ጥቃት ለተጎዱ ማኅበረሰቦች ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚያልም ነው፡፡ እነዚህም፡

ሀ. የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎችን እና ጥቃት ፈጻሚዎችን በማናገር ጊዜ በነገረ መለኮት ተማሪዎች እና በካህናት በኩል የተሻለ ዝግጁነት እንዲኖር፣ 

ለ. ፕሮጀክቱ በሚሠራባቸው ሀገራት ባሉ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል አካላት ዘንድ ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ ትኩረትን ማሳደግ፣

ሐ. በደንብ የተደራጀ የቤት ውስጥ ጥቃት ዘዴ እናም ጥቃት ቢደርስበትም በተሻለ ሁኔታ አገልግት የሚያገኝ ማኅበረሰብ፣

መ. የጋራ ተጠቃሚነት ያለበት አጋርነት እና የተሳትፎአቸውን ሁኔታ ከግምት ያላስገባ ለተለያዩ የቡድኑ አባላት የሚሆን ሙያዊ ዕድገት፡፡

ስለ ፕሮጀክቱ የበለጠ ለማወቅ ዋናዋን ተመራማሪ ዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ በዚህ (ri5@soas.ac.uk) ወይም በፕሮጀክቱ ኢሜል በዚህ ያግኟት (soasflf@soas.ac.uk)፡፡