Coming soon!

This language is currently in review and will be available soon!

ስለ እኛ

የዚህ ፕሮጀክቱ ፈጣሪና ምሪ የሆኑት ዶ / ር ሮሚና ኢስትራቲ በቅኝ ገዥ ጥናት ተመራማሪ እና ሰዎችን ማዕከል ያደረጉ ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስሜታዊ የሆኑ የሥርዓተ-ፆታ እና የልማት ጣልቃ-ገብነትን በማዳበር ረገድ ከአስር ዓመት በላይ ልምድ ያካበቱ ናቸው ፡፡

ፕሮጀክቱ የተዘጋጀው እና የሚመራው ሕዝብ ተኮር የሆኑ እና ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ ትኩረትን የሚጨምሩ ጾታዊና የዕድገት ጣልቃ ገብነቶችን በማዘጋጀት ከዐሥርት ዓመታት በላይ ልምድ ባላቸው ከቅጅ አገዛዝ ነጻ የሆነ ጥናት ተመራማሪ እና የትግበራ ባለሙያ በሆኑት በዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ ነው፡፡

ዶ/ር ኢስትራቲ በዚህ የምርምር ፣ የማነቃቂያ እና የዕውቀት-ልውውጥ እንቅስቃሴዎችን የመምራት እንዲሁም ከአጋሮች ፣ ከሥራ ባልደረቦች እና ከባለድርሻ አካላት ማኅበረሰቦች ጋር ምርታማ የሆነ በዕድገት እና በእምነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን የማጎልበት ቀጥትኛ ኃላፊነት አለባቸው ፡፡ ይህን ፕሮጀክት በማስተዳደር ረገድ ዶ/ር ኢስትራቲ  የትርፍ ሰዓት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ በሆኑት በወ/ሮ እስተላ ፓፓያኒ ይታገዛሉ፡፡

  • የአክሱም ዩኒቨርሲቲ አክሱም ኢትዮጵያ

 

  • ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ መቀሌ፣ ኢትዮጵያ

 

 

 

 

  • የእንግሊዝ ብሪስቶል እና ሸፊልድ ዩኒቨርስቲዎች: 

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው የፕሮጀክቱ ክፍል በሁለት ተባባሪ ተመራማሪዎች የሚደገፍ ነው

ሀ) ፕሮፌሰር ፓርቬን አሊ፡ የነርሲንግ እና አዋላጅ መምሪያ ክፍል ፣ የጤና ሳይንስ ትምህርት ቤት ፣ የሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ለ) ፕሮፌሰር ጂን ፌደር የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ክትትል ማእከል፣ ብሪስቶል የጤና ትምህርት ቤት፣ የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የሥራ ድርሻቸው በሥልጠና ዙሪያ በማማከር እና የፕሮጀክቱ ተመራማሪን በሙያ ማሳደግ ላይ በሆኑ  በውስጥ እና በውጭ አማካሪዎች ይደገፋል፡፡

  • ዶ / ር ኤርሚያኒያ ኮሉቺ : ተባባሪ ፕሮፌሰር  በእይታ እና በባህል ሳይኮሎጂ ፣ ሚድልክስ ዩኒቨርሲቲ በለንደን ፣በዩናይትድ ኪንግደም
  • ዶ / ር ሊሳ ፎንቴስ ፡ ሁለገብ ትምህርት ዋና መምህር ፣ በአሜሪካ ማሳቹሴትስ አምኸርስት
  • ፕሮፌሰር ሊንዲው ዶቨይ፡ በ ፊልም እና ስክሪፕት ጥናት ፕሮፌስር፣ ሶአሰ ሎንደን ዩኒቭርስቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ፕሮጀክቱ በሌሎች ገለልተኛ ባለሙያዎችም ይደገፋል ይህም የነገረ መለኮት አጥኚዎች፣ ተርጓሚዎች፣ የሥነ ልቦና አሠልጣኞች እና ፕሮጀክቱን የሚያግዙ ባለሙያዎችን ያካትታል፡፡

አቶ ኤልያስ ገብረሥላሴ፡ የቅድስ ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ምሩቅ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤ በአጎራ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ፣ ዩ ኤስ ኤ (ኦንላይን)

ወ/ት ሰላማዊት ረታ፡ የቅድስ ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ምሩቅ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤ በአጎራ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ፣ ዩ ኤስ ኤ (ኦንላይን)

ወ/ት ሊያ ደስታ፡ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ፣ የምግብ ጥበቃ ማእከል፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አቶ ይሄይስ ዮሐንስ፡ የአባ ፍሬምናጦስ ከሳቴ ብርሃን የነገረ መለኮት ኮሌጅ ምሩቅ፣ መቀሌ፣ ኢትዮጵያ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሉ አየለ፡ የሥነ ለቦና አማካሪ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ የሳይኪያትሪ (የአእምሮ ህክምና) ክፍል (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ወ/ሮ ቤዛ ብርሃኑ፡ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትህርት ምሩቅ፣ የሕግ ጠበቃ እና አማካሪ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ዶ/ር ኃይለ ገዛኢ ፣ የትግርኛ መምህር ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ አዲስ አበባ ኢትዮዽያ

አቶ ፍሪሰንበት ጂ. የ. ኣድሓኖም፣ Bsc በ Computer Engineering, Data Analyst፣ MTh ተማሪ በ ኣጎራ ዩኒቨርሲቲ ኣመሪካ (Virtual)

ወ/ሮ የሺሃረግ ኣበበ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራቂ ፣ ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ወ/ሮ ፀገነት ኃይለመቅያል፣  BA በ Organizational Leadership, Minor in Business Administration & Certificate in Communication ፤ ከ ዩኒቨርሲቲ ሲንሲናቲ ሕቡራት መንግስታት ኣመሪካ፤ ኣዲስ ኣበባ  ኢትዮዽያ

አቶ ዴቪድ ፖትረል፡ ፒክ ዲዛይን ኤጀንሲ በዩናይትድ ኪንግደም፡ ዌብሳይቱን የሠራ (በዚህ ያግኙት https://peak.agency)

አቶ ዳንኤል ደስታ ኅሉፍ፡ ዲዲኤን ማስታወቂያ በኢትዮጵያ፣ የፕሮጀክቱን ቪዡዋል አይደንቲቲ የሠራ (በዚህ ያግኙት d2dproduct@gmail.com)

ወ/ት ራሄል ደንካን፡ የኦንላይን ኅትመት ውጤቶችን የማጥራት ንባብን በማገዝ፣ ደንካን የማጥራት ንባብ በዩናይትድ ኪንግደም (በዚህ ያግኙ፡ www.duncanproofreading.com)

በዓመት ሁለቴ  የሚገናኝ የአማካሪ ቦርድ የፕሮጀክት ተመራማሪውን  እና ቡድኑንበስትራቴጂክ አቅጣጫ ያማክራል ፣ እንዲሁም በእያንዳንዱ ጥናት ዐውድ እና የባለድርሻ አካላት ትርጓሜዎች እና ፍላጎቶች መሠረት ከፍተኛውን ውጤት እንዲያመጣ ፕሮጀክቱን ይከታተላል ፡፡ የቦርዱ አባላት ከተለያዩ ዘርፎች እና ልዩ ልዩ ሙያዎች ፣ የሙያ ደረጃዎች ፣ ብሔረሰቦች እና የእምነት ባሕሎች የመጡ ናቸው ፡፡ በፕሮጀክቱ ሀገሮች ውስጥ ፕሮጀክቱ እየሰፋ ሲሄድ አዳዲስ አባላትም ተጋብዘዋል ፡፡ የአሁኑ አባላት ዝርዝር ከዚህ በታች ቀርቧል፡

ፕሮፌሰር ናንሲ ናሰን-ክላርክ፡ ኤሜሪታ ፕሮፌሰር፣ ኒው በብራንስዊክ ዩኒቨርሲቲ፤ የ አር ኤ ቪ ኢ ፕሮግራም ዋነኛ ተመራማሪ፣ ካናዳ

ወ/ሮ  ሜንዲ ማርሻል፡ የጾታ ፍትህ ዳይሬክተር፣ አንግሊካን ኅብረት ቢሮ፤ የቻሪቲ ሪስቶርድ መሥራችና የቀድሞ ረዳት ዳይሬክተር፣ ለንድን፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ወ/ሮ  ሁዳ ጃዋድ፡ የእምነት እና ማኅበረሰብ ፕሮግራም ማናጀር፣ ስታንዲንግ ቱጌዘር፤ የሴቶች ጥቃት ይቁም ማኅበር ረዳት ሰብሳቢ፣ ለንድን፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ወ/ት ሳፋ አሊ፡ በፕሮፌሽናል ሥልጠናዎች የሥነ ልቦና አማካሪ፣ ስኩል ኦፍ ኢንቫይሮንመንት፣ ትምህርትና ዕድገት፣ ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

አቶ ማሕሙድ አሻል፡ የሥስተኛ ዲግሪ ዕጩ፣ የሃይኖት ጥናቶች፣ የላንክስተር ዩኒቨርሲቲ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ዶ/ር ያ አሳሬ፡ ዳይሬክተር፣ ዳይቨርሲቲ ሪሶርስ ኢንተርናሽናል (DRI)፣ ብራይተን፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ወ/ሮ ፌቨን አርአያ፡ የፕሮግራ አስተባባሪ፣ ነን ስቴት አክተር ኮአሊሽን (NSAC)፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አቶ ናሆም ኪሮስ፡ የጥናት አጋዝ እና መምህር፣ ኦርታ የጤና ሳይንስ እና ሜዲሲን ኮሌጅ፣ የማኅበረሰብ ሜዲሲን ክፍል፣ አስመራ፣ ኤርትራ

ዶ/ር ክርስቲን አኡን፡ በኮቨንትሪ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የእምነት (trust)፣ ሰላም እና ማኅበራዊ ግንኙነት ማእከልሲኒየር የጥናት ቡድን አባል እና የእምነት (faith) ሰላማዊ ግንኙነቶች የጥናት ቡድን መሪ፣ ኮቬንትሪ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

አቶ ፍሬዘር በንቲ፡ የኢኦተቤ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊሎሶፊ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አቴ ኅሉፍ ወ/ሥላሴ ካህሳይ፡ በሰላምና ዕድገት ማእከል ሲኒየር የፕሮግራ ማናጀር፤ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ማኅበር የቀድሞ ምክትል ዋና ጸሐፊ (IRCE)፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ወ/ሮ ወሰን ክፍሌ፡ በFORWARD፣ የፕሮግራም ልማት እና አጋርነት ስራ አስኪያጅ፡ እንግሊዝ ሀገር