Coming soon!

This language is currently in review and will be available soon!

ተጽእኖ

ተጽእኖን የምንረዳበት ሁኔታ

ፕሮጀክቱ የሚነሣው ተጽእኖ ከዚህ ቀደም ምዕራባውያን ተኮር በሆነ ቀድሞ በተወሰነ ወይም አርቆ በማይመለከት መልኩ በብዙ ዓይነት መንገድ የተበየነ መሆኑን ከመረዳት ሲሆን ከዚህ አረዳድም ለመለየት ያልማል፡፡ የኛ ዋነኛ መነሻ ዐሳብ ትርጉም ያላቸው እና ለውጥ የሚያመጡ ጣልቃ ገብነቶች የሚመነጩት በተግባራዊ ማረጋገጫ እና በቀጥታ በመሳተፍ ከታች ወደ ላይ ሲተገበሩ ነው የሚል ነው፡፡ በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ የሚሠሩ ጥናቶች በምዕራባውያን ተኮር ወይም ዓለም አቀፍ በሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት መነሾዎች ላይ የተንተራሱ ከሆኑ እና ግለሰቦች እና ማኅበረሰብ ላይ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ በኑሮ ከሚያጋጥሙ እውነታዎች የራቁ ከሆኑ ለግለሰቦቹም ሆነ ለማኅበረሰቡ የሚኖራቸው ፋይዳ ጥያቄ ላይ ይወድቃል፡፡

ይሄ ፕሮከጅት የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚያስቀጥሉ እውነታዎችን ለመረዳት በምእመናን እና በካህናት ላይ በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ የተሠራ ጥናት ውጤት ነው፡፡ የተገኘው ልምድም ካህናት የቤት ውስጥ ተጠቂዎችን እና ጥቃት ፈጻሚዎችን በአግባቡ መቅረብ እንዲችሉ ዝግጁነታቸውን መገንባት እንደሚያስፈልግ የጠቆመ ሲሆን አዎንታዊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ዓለማዊ እና ሃይማኖታዊ ባለድርሻ አካላትን በማዋሐድ በአግባቡ የተደራጀ የቤት ውስጥ ጥቃትን የመከላከል ዘዴ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም አሳይቷል፡፡

እንዲህ ያሉ ማኅበረሰብ ላይ የተመሠረቱ እና ማኅበረሰብን ያዋሐዱ አቀራረቦች ያለ አጥኚዎች እና  የትግበራ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና የአከባቢው ማኅበረሰብ እገዛ፣ ሙያዊ ድጋፍ እና መልካም ፈቃድ ሊሳኩ እንደማይች እንረዳለን፡፡ ቡድንነትን ማሳደግ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ተጽእኖ የመፍጠር ዓላማን ይይዛል፡፡

ምንም ስንኳ ፕሮጀክቱ የሚመራው በተከታይ ከሚዘረዘሩት ሦስት ዓላማዎች በሚመነጭ ዝርዝር የተጽእኖ መርህ መሠረት ቢሆንም በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ዮናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ የፕሮጀክቱ ተሳታፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና ማኅበረሰቦች ጋር ባለ መስተጋብር ሁኔታዎችን ለመቀበል እና አዳዲስ ግብአቶችን ለመጠቀም ካለ ፍላጎት የ‹ተጽእኖ›ን ትርጉም በፕሮጀክቱ ክንውን ጊዜ ሁሉ ታስቦበት ለምርምር ክፍት እንዲሆን አግርጓል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማዎች እና የተጽእኖ ስልት

ሀ. ሀገረኛ አመለካከቶችን ለሚያስቀድም እና የጋራ ተጠቃሚነት ያለበትን የጥናት አጋርነት ለሚያበረታታ የቤት ውስጥ ጥቃት ጥናት ከቅኝ አገዛዝ ነጻ የሆነ አቀራረብን እንዲከተል ማጠንከር፣

ለ. በተለይ በቤት ውስጥ ጥቃት ጥናት እና ትግበራ ላይ ሃይማኖታዊ-ባሕላዊ እና ሥነ ልቦናዊ መመዘኛዎችን ማዋሐድ እና በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ላይ የሚስተዋሉ ሃይማኖዊ-ባሕላዊ ስሜታዊነቶችን ማሻሻል፣ 

ሐ. የተጎዱ አካላትን የአደጋ ተጋላጭነት ከመቀነስ በተጓዳኝ ለቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች እና ፈጻሚዎች አግባብ ያለው ምላሽን መስጠት ይችሉ ዘንድ አግባብ ባለው ዐውድ የሃይማኖት ሰዎችን ማስታጠቅ፡፡ 

ሀ. ከፕሮጀክቱ አጋሮች ጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር በምንሠራት ጊዜ የውይይትን መንገድን መከተል፣

ለ. በጥናት እና ለውጥ አምጪ መርሐግብሮች ጊዜ አሳታፊ፣ ባሕላዊ እና ማኅበራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ እና ሕዝብ ተኮር የሆነ መንገድን መከተል፣

ሐ. በኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የቡድን አባላቶች በሙሉ የሚሻሻሉበትን ዕድል ማመቻቸት፡፡

ሀ. ሥልታዊ በሆነ የጽሑፍ ሥራዎች ግምገማ እና ከየቤት ውስጥ ጥቃት ተጠቂዎች እና ፈጻሚዎች ጋር በሚደረግ አዲስ ጥናት በሃይማኖታዊ መለኪያዎች፣ በሰው ሥነልቦና እና የቤት ውስጥ ጥቃት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ማስረጃ መገንባት፣

ለ. ሃይማኖታዊ-በሕላዊ መለኪያዎች መንግሥት መር በሆኑ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ በቤት ውስጥ ጥቃት ላይ በሚሠሩ ቡድኖች ላይ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ያውን ግንዛቤ በሥልጠና፣ ግንዛቤን በሚጨምሩ ዝግጅቶች እና በቀጥታ ግንኙነት ማሻሻል፣

ሐ. በቡድኖች፣ በትምህርት መስኮች እና በባለድርሻ አካላት መካከል በዕውቀት ሽግግር እንቅስቃሴዎች እና በማኅበራዊ መስተጋብሮች አማካኝነት መማማሮች እንዲኖሩ ዕድሎችን እና መድረኮችን መፍጠር፡፡

ሀ. በካህናት ትምህርቶች ላይ እና በአባታዊ የማስታረቅ አገልግሎታቸው ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በተመለከተ ያለውን መረዳት ለመጨመር እና ለካህናት የሚዘጋጁ ሥርዓተ ትምህርቶችን እና ሥልጠናዎችን ለማሻሻል ከካህናት፣ የነገረ መለኮት መምህራን እና የነገረ መለኮት ተማሪዎች ጋር መሥራት፣

ለ. ካህናት ጾታዊ ግንኙነትን፣ ጋብቻን እና የቤት ውስጥ ጥቃት በተመለከተ ነገረ መለኮታዊ ዕውቀትን እንዲታጠቁ እና በማኅበረሰባቸው ውስጥ ያለውን የቤት ውስጥ ጥቃት ችግር በአግባቡ እንዲረዱ ብሎም ችግሩን ከማስቆም ወይ ከማስቀጠል አንጻር የነርሱን ድርሻ እንዲረዱ ለማስቻል አሳታፊ እና ዐሳባቸውን ማንጸባረቅ የሚችሉበት ዎርክሾፕ ማዘጋጀት፣

ሐ. ካህናትን፣ የነገረ መለኮት ሊቃውንትን እና የነገረ መለኮት ተማሪዎችን ስለ የድጋፍ ሥርዓቶች እና ስለ ዓለምአቀፋዊ የጥበቃ ፕሮቶኮሎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ ያሉ አገልግሎቶች ላይ ሀገራዊ የሕግ፣ የሥነልቡና እና ሌሎች ሙያዎችን ማካተት፡፡