This language is currently in review and will be available soon!
ፕሮጀክት ድልድል በባለ ድርሻ አካላት እና በሚመለከታቸው አካላት መካከል ትብብር እንዲኖር በማስተባበር እና በባሕሎች መካከል በደቡብ-ሰሜናዊ የእውቀት ሽግግር መንገድ የእርስ በእርስ መማማሮች እንዲኖሩ በማበረታታት ተጽእኖውን ከግብ ለማድረስ ያልማል፡፡ በተለይም በቤት ውስጥ ጥቃትና ጾታ ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ላይ በሚሠሩ ምርምሮችና ትግበራዎች ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የንድፈ ዐሳብ መርሖችን በማዘጋጀት እና ትግበራዎችን በመወሰን የምዕራቡ ዓለም ማኅበረሰብ ያለውን ታሪካዊ የበላይነት ለመቀየር ከፍ ያለ ፍላጎት አለን፡፡
ለድረ ገጹ የሚሆኑ አበርክቶዎችን ከተመራማሪዎች፣ ከባለሙያዎች፣ ከሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ ከማኅበራዊ ሠራተኞች፣ ከቀሳውስት፣ ከነገረ መለኮት ተማሪዎች ከመላው ዓለም በሁሉም ዓይነት ቋንቋ እንዲመጡ እንጋብዛለን፡፡ አበርክቶውም ተግባራዊ ጥናት፣ ከድርጅት መርሐግብሮች የተገኙ ትምህርቶችና ግኝቶች፣ ከመስክ ሥራ የተገኙ ሥነ ሰባዊ ልምዶች፣ ወይም ልናገናኛቸው በምንፈልጋቸው ኅብረ ብሔራዊ ባለ ድርሻ አካላት ማኅበረሰቦች ውስጥ በጥልቀት ማሰብን የሚያነሣሱ አስተያየት ጋባዥ ጉዳዮች ላይ ሊሆን ይችላል፡፡
ከምንደግፋቸው እና ከምናግዛቸው (Decolonial Subversions የሚለውን ተመልከት) ሌሎች የቅኝ ከተገዛ አስተሳሰብ ነጻ የመውጣት ጅማሮዎች በተጨማሪ የጽሑፍ፣ የድምጽና የምስል አስተዋጽኦዎችን ፖስተሮችን፣ ግጥሞችን እና የድረ ገጽ የድምጽ ቅጂዎችን እንቀበላለን፡፡ የምስልና የድምጽ አበርክቶዎች ከ Decolonial Subversions የተወሰደውን ከታች የተቀመጠውን የማስገቢያ ደንብ የተከተሉ መሆን አለባቸው።
ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ለድረ-ገጽ የሚሆን ጽሑፍ የማስገባት ፍላጎቱ ካላችሁ ስለ ዐሳባችሁ ለመወያየት እና የማስገቢያ ጊዜ ላይ ለመስማማት ለፕሮጀክቱ በተዘጋጀው የኢሜል አድራሻ soasflf@soas.ac.uk ያግኙን፡፡
የጽሑፍ ርዝመት፡ አበርክቶው በ800 እና 1200 ቃላት መካከል መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ለሚረዝም አበርክቶ የሚቻለውን ለማድረግ ከቡድኑ ጋር ይነጋገሩ፡፡
የአበርክቶ ዝርዝር፡ ሁሉም አበርክቶዎች በወርድ ፋይል፣ በታይምስ ኒው ሮማን፣ በ12 ፎንት እና በደብል ስፔስ መሆን አለባቸው፡፡ ማጣቀሻ በበቂ የኅዳግ ማስታወሻ መደገፍ አለበት፡፡ ጸሐፊዎች በሁሉም አንባቢዎች በተለይም ከዩናይትድ ኪንግደም ውጪ በሚገኙ አንባቢዎች በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ማጣቀሻዎችን እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ፡፡ የጀርባ ማጣቀሻ አጻጻፍ የ APA Referencing Style ን መከተል አለበት፡፡ ከሌላ ምንጭ ቀጥታ የተወሰዱ ዐሳቦች (ለምሳሌ ምስክርነቶች) በትምህርተ ጥቅስ (inverted commas) ውስጥ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ከዐርባ ቃላት በላይ የሆኑ ከሌላ ምንጭ ቀጥታ የተወሰዱ ዐሳቦች በቀኝና በግራ አንዳንድ ሴንቲ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ማለት እና የፊደል ቅርጽና መጠናቸው ተመሳሳይ የሆኑ መሆን ያለባቸው ሲሆን ትምህርተ ጥቅስ መጠቀም አያስፈልግም።
የእንግሊዘኛ ፊደል አጠቃቀም ስምምነትን በተመለከተ የዘዴ መመሪያውን (style guide) ተመልከት፡፡ በሌሎች ቋንቋዎች የፊደል አጠቃቀም ስምምነት መርህን አላስቀመጥንም ነገር ግን ጸሐፊያን ወጥ የሆነ የአጻጻፍ ዘዴን እና የፊደል አጠቃቀምን እንዲከተሉ ይጠበቃሉ፡፡
የሥነ ምግባር መለኪያዎች፡ ሁሉም ይዘቶች መዘጋጀትና መቅረብ ያለባቸው ልክ በዓለም አቀፍ የቤት ውስጥ ጥቃት ምርምር እና ትግበራ ላይ እንደሚጠበቀው ጥብቅ በሆነ የሥነ ምግባር እና ጥበቃ መለኪያ መንገድ ነው፡፡ በተሳታፊው በድረ-ገጽ ጽሑፉ ጥቅም ላይ የሚውለው መረጃ መሰብሰብና መተግበር ያለበት ነባሩን የመረጃ አጠባበቅ ሕግ በተከተለ መንገድ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ መለኪያዎች ምን እንደሆኑ የማያውቁ ከሆነ አበርክቶ ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ተሳታፊዎቹ የፕሮጀክቱን ቡድን ማግኘት አለባቸው፡፡
ፈቃድና የቅጂ መብት፡ አበርክቶዎች በጸሐፊው የሚታወቁ ሲሆን የሚታተሙት በ website’s Creative Commons Attribution-NonCommercial (CC BY-NC 4.0) ዓለም አቀፋዊ የሕዝብ ፈቃድ (International Public License) ነው፡፡ ይሄ ማለት ጸሐፊዎች በሥራቸው ላይ ሙሉ የባለቤትነት መብት ያላቸው ሲሆን ሥራቸውን መጀመሪያ ላይ የሚያሳትሙት (ለንባብ የሚያበቁት) ግን በፕሮጀክቱ ድረ-ገጽ ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም የጽሑፍ ሥራው ከንግድ ዓላማ በቀር በአግባቡ በማጣቀሻ ከማሳወቅ ጋር በማንኛውም አመክንዮ በድጋሚ አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ይሄ ፈቃድ ጸሐፊው ጽሑፉን ለንግድ ባልሆነ መንገድ መልሶ ዐሳብ እንዲጨምርበት እና ለፕሮጀክት ሥራው ተስማሚ አድርጎ እንዲያቀርበው ያስችለዋል፡፡ አዲሱ ሥራ ለፕሮጀክቱ ድረ-ገጽ የመጀመሪያ አታሚነት እውቅና መስጠት ያለበት ሲሆን ጥቅም ላይ መዋል ያለበትም ከንግድ ዓላማ ውጪ በሆነ መንገድ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን የግኝት ሥራዎች በተመሳሳይ መመዘኛ አይደለም ፈቃድ ማግኘት ያለባቸው፡፡
የአስተዋጽኦ ዓይነቶች፡ የድምጽ አበርክቶዎች የድረ ገጽ የድምጽ ቅጂዎች፣ መዝሙሮች፣ የቃል ታሪኮች፣ ግላዊ አስተያየቶች፣ የሰው ዘር መዛግብት፣ ቃለ መጠይቅ ወይም የተቀዱ ንግግሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የምስል አበርክቶዎች አንድ ወይም የብዙ ፎቶዎች ስብስቦች፣ ሥዕሎች፣ፖስተሮች ወይም የመረጃ ሥዕሎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የጽሑፍ ሥራው ርዝመት፡ የድምጽ ቅጂዎች ከ20 ደቂቃ መብለጥ የለባቸውም (ቀድሞ የሚረዝምበት ምክንያት ካልተገለጸ በቀር)፡፡ የምስል አበርክቶ በአጫጭር ምስሎች የተደገፉ እና ስለ ምስሎቹ ገላጭ የሆኑ ማብራሪያዎች ያካተቱ 10 ምስሎችን መያዝ አለበት፡፡ ሁሉም አበርክቶዎች ፕሮጀክቱ እና የድረ-ገጽ ይዘቶቹ የሚያተኩሩባቸውን አቅጣጫዎች እንዴት እንደሚቀርቧቸው የሚያብራሩ መሆን አለባቸው፡፡
የማስገቢያ መንገድ፡ ለድምጽ አበርክቶዎች አበርካቾች የይዘቱ ፈጣሪ እንደሆኑ የሚገልጽ ነጻ የሆነ አካውንት በሳውንድ ክላውድ (Soundcloud) እንዲከፍቱ ይመከራል፡፡ የድምጽ ቅጂዎች ያለ ኢንተርኔት በግለሰቡ የመቅጃ ዕቃዎች መቀዳት የሚችሉ ሲሆን ተቀባይነት ባላቸው መንገዶች በሳውንድ ክላውድ (Soundcloud) ላይ መጫን (መታተም) አለባቸው፡፡ አንዴ ከተጫኑ በኋላ በፕሮጀክቱ ድረ-ገጽ ላይ እንዲወጡ (እንዲታተሙ) አበርካቾቹ ሊንኩን ኮፒ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ቡድን መላክ አለባቸው፡፡ የምስል አበርክቶዎች መላክ ያለባቸው የ MS Office ጥቅሎችን በመጠቀም በተፈጠረ (ያም በወርድ፣ በኤክሴል ወይም በሌላ የንድፍ መሳርያ) በ jpeg (or jpg) መልክ መሆን አለበት ይሄም ከፍተኛ ጥራትና ለማረጋገጥ የሚደረግ ነው፡፡