Coming soon!

This language is currently in review and will be available soon!

ካህናት እና የነገረ መለኮት ተማሪዎች

መረጃዎች

ድልድል ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማኅበረሰብ ውስጥ ካሉ ምእመናን እና ካህናት እና በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ምእመናን ጋር አስቀድሞ ተሠርቶ ለተጠናቀቀ የጥናት ሥራ ምላሽ ይሰጣል፡፡

በብዙ ሃይኖዊ ሁኔታዎች እንደምንገነዘበው በገጠሩ መኅበረሰብ ውስጥ ያሉ የኦርቶዶክስ ካህናት የሥነ መለኮት ግንዛቤ ደረጃቸው ላይ እ አባታዊ ድጋፍ በብዛት የመስጠት ዐቅማቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ በሚያሳድር መልኩ የተለያዩ ውስንነቶች ይስተዋልባቸዋል ብሎም ለዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች የተጋለጡ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ካህናት ለባትዳሮች መንፈሳዊ አባቶች ስለሚሆኑ የተለያዩ በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ጨምሮ ለአጠቃይ ትዳር ነክ ችግሮች የመጀመርያው አማካሪ ሆነው ይታያሉ፡፡ በአብዛኛው ለችግሩ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጎጂ ባሕላዊ ልማዶችን እና እምነቶችን ይቃወማሉ፡፡ እንዲሁም በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ለማሸማገል በመሞከር ሴቶቹን ከአደገኛ ሁኔታዎች እንዲወጡ ይረዷቸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ የችግሩን እውነተኛ ዳራ እና የሄዱባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች በምእመናን ላይ የሚያሳድሯቸውን ተጽእኖዎች ችላ ይላሉ፡፡ በተጨማሪም የተጠቀሟቸው መንገዶች ምን ያህል በአፈታሪካዊው ባሕል እና አረዳድ ውስጥ ሥር ሰደው እንደተቀመጡ አያስተውሉም፡፡ ይሄ ሁኔታ ደግሞ በራሱ በትዳር ውስጥ ያሉ አንዳንድ የጥቃት ዓይነቶች እንዲቀጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡

በዚህ ክፍል ሥር ያሉ ምንጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካህናት በጾታዊ ጉዳዮች፣ በትዳር እና በጥንዶች አብሮነት ላይ ያላቸውን የነገረ መለኮት ግንዛቤ በማነፅ እነዚህን የተወሳሰቡ ሁኔታዎች እንዲረዱ እንዲሁም በችግሮቹ መቀጠል እና መቀረፍ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲገነዘቡ ለማገዝ ያልማሉ፡፡ በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጸም ጥቃትን በተመለከተ ለጥቃቱ ሰለባዎች፣ ተራፊዎች እንዲሁም ለአጥቂዎች ድጋፍ ለመስጠት ሲያስቡ ሊያውቋቸው የሚገቡ አደጋን የመከላከል ዘዴዎችን እና ሥነልቦናዊ ዳራዎችን ለማሳወቅ ይጥራሉ፡፡

ምንጮቹም በኢትዮጵያ የተካሄዱ አጠቃላይ ጥናታዊ ሥራዎችንና ከካህናት ጋር የተደረጉ አሳታፊ የመስክ ናሙናዎችን ያካትታሉ፡፡ ምንም ስንኳ የተጠቀሱት ግኝቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ውስን ማኅበረሰቦችን ብቻ የተመለከቱ ቢሆኑም እነዚህ ግብአቶች ለሰፊው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በውጭ ለሚገኙ ካህናት፣ የነገረ መለኮት ሊቃውንት እና ተማሪዎች ጥቅም መዋል እንዲችሉ ጥረት ተደርጓል፡፡    

የእኛ መረጃዎች

የይዘት ማጠቃለያ - ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ጋር በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ የሚደረግ ዐውደ ጥናት

በድልድል ፕሮጀክት

ሰኔ 2013

ይሄ የሥልጠና መጽሔት በኢትዮጵያ አማራ ክልል ለሚገኙ ቀሳውስት የተሰጡ ሥልጠናዎችን ዋነኛ ይዘት ጠቅልሎ የሚያቀርብ ነው፡፡ ዋነኛ ትኩረቶቹም የኦንላይን ድረገጹን የመጠቀም ዕድሉ ያላቸው በሀገሪቷ የሚገኙ ካህናት ናቸው፡፡ የሥልጠና መጽሔቱ የተዘጋጀው በወርክሾፑ ላይ በሚገኙ ርእሶች እና ጭብጦች መሠረት ቢሆንም አጭርና ግልጽ ለማድረግ ሲባል የመወያያ ጥያቄዎችና የቡድን እንቅስቃሴዎች ተዘለዋል፤ በርከት ያሉ ርእሶችም ቀለል ያለ አቀራረብ እንዲይዙ ወይም እንዲያጥሩ ተደርጓል፡፡ ይሄንን የሥልጠና መጽሔት የሚጠቀሙ ካህናት በማኅበረሰባቸው ውስጥ መንፈሳዊ ድጋፍ በሚያደርጉበት ወይም በሚያስተምሩበት ጊዜ የመረጡት ይዘት ላይ የራሳቸውን አረዳድ እንዲጨምሩበት እና ወደ ማኅበረሰቡ ነባራዊ ሁኔታ እንዲያመጡት ይመከራሉ፡፡

Content Summary: Workshops on Domestic Violence with Ethiopian Orthodox Täwahәdo Church (EOTC) Clergy

Project dldl/ድልድል

June 2021

The current booklet summarises the main content of workshops delivered with Ethiopian Orthodox Täwahәdo clergy in Amhara region, Ethiopia.  The booklet is targeted at clergy around the country who have access to the online platform. The booklet is structured according to the topics and themes covered during the workshop, however, for the sake of brevity, discussion questions and group activities are omitted, while many topics are simplified or abbreviated. Clergy using this booklet are advised to use their discretion and to contextualise appropriately the content they choose to use when providing spiritual support or teaching in their communities.

[ትምህርተ ሕይወት] የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እምነትን፣ ጋብቻን እና በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ጥቃትን በተመለከተ የሚያስተምሩት ትምህርት እና ተግባራቸው:- በትግራይ ክልል በአክሱም ያለው ሁኔታ (ከጦርነቱ በፊት)

ጸሐፊ፡ ዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ (Dr Romina Istratii)

ተርጓሚዎች፡ ኤልያስ ገብረሥላሴ (Elias Gebrselassie) እና ፍሬሰንበት ገ/ዮሐንስ

June 2021 (ሰኔ 2013)

የትግበራ ጽሑፉ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ ዘንድ በጋብቻ ውስጥ ያለ ጥቃትን በተመለከተ በተሠራ የጥናት ምርምር ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ጥናቱ የምእመናንን ሕይወት፣ በጾታዊ መመዘኛዎች እና ልማዶች መካከል ያለውን ግንኙነት እና በዚህ ሃይማኖተኛ ማኅበረሰብ ውስጥ በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ጥቃት በመቀጠሉ እና በመገታቱ መካከል ያለውን ውስብስብ ግንኙነት ከመረዳት አንጻር የእምነትን እና የሃይማኖት ልምምድ ያላቸውን ወሳኝነት አሳይቷል፡፡ እምነት የጥቃት ፈጻሚነትን ጠባይ እና በጋብቻ ውስጥ ከሚኖር ጥቃት ጋር በተያያዘ ያሉ ልማዶችን ለመከላከል ወይም ለማስቆም ውስብስብ በሆነ መንገድ ለንጽጽር በቀረበበት ሁኔታ ጥናቱ በነገረ መለኮት እና ባሕላዊ አረዳድ መካከል ያለውን ወሳኝ የሆነ ውጥረት ገልጧል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና የነገረ መለኮት ሊቃውንት፣ የመንግሥት አካላት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት መከላከል  አገልግሎት ሰጪዎች እምነትና የሃይማኖት ልምምድ በምእመናን የጋብቻ ሕይወት ውስጥ ያላቸውን ውስብስብ ሚና፣ በጋብቻ ውስጥ የሚኖር ጥልን ለማስታረቅ ቀሳውስት የሚከተሉት መንገድን በተመለከተ እና ችግሩን ለመቅረፍ ነገረ መለኮትና የኖላዊነት አገልግሎት እንዴት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ለማስገንዘብ በሚደረግ ጥረት ይሄ የጽሑፍ ሥራ የዚህን የተጠናቀቀ የጥናት ውጤት ዋና ዋና ግኝቶች ለብዙሀኑ ለማድረስ ያልማል፡፡

Discourses and Practices of Ethiopian Orthodox Täwahәdo Clergy Regarding Faith, Marriage and Spousal Abuse: The Case of Aksum in Tigray Region (prior the war)

Dr Romina Istratii

June 2021

The current working paper is informed by previous ethnographic investigations of conjugal abuse in the Ethiopian Orthodox community in Tigray region in northern Ethiopia. The research evidenced the importance of religious beliefs and experience in understanding the life of the laity, intersections with gender parameters and norms, and complex associations with the continuation and deterrence of conjugal abuse in this religious society. The study revealed important tensions between theological and folklore understandings, with ‘faith’ being juxtaposed in complex ways to ‘culture’ to preserve or discontinue pernicious behaviour and norms associated with conjugal abuse. The current working paper aims to improve understanding among Ethiopian Orthodox Täwahәdo Church clergy and theologians, state agents, and non-governmental domestic violence stakeholders about the complex role of religious beliefs and experience in the married lives of the laity, about the clergy’s approaches to mediation in marital conflict, and to suggest how theology and pastoral interventions may be appropriately engaged in alleviating the problem.

ለኦርቶዶክስ ጋብቻ መመሪያ፣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች ስለ ወንድ እና ሴት፡የትዳር ሕይወትና የትዳር ላይ ጥቃት

ጸሐፊ፡ ዶ/ር ሮሚና ኢስትራቲ (Dr Romina Istratii)

ተርጓሚዎች፡ ኤልያስ ገብረሥላሴ (Elias Gebrselassie) እና ፍሬሰንበት ገ/ዮሐንስ አድሃኖም (Fresenbet Gebreyohanns Adhanom)

March  2021 (ጥር 2013)

ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰባት ስብከቶች የተውጣጣ ሲሆን፤ በወንድ እና ሴት የጋብቻ ሕይወት ላይ ያጠነጥናል፡፡ ስብከቶቹንም በምልከታ እና ልምድ በዳበረ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ (ፍሮኒማ) ለመመልከት ሙከራ ተደርጓል፡፡ ዓላማውም የቤተክርስቲያን አባቶች አስተምህሮን ለምዕመናን ነባራዊ ሁኔታዎች የበለጠ በማቅረብ ስለ ኦርቶዶክሳዊ እምነት ያላቸውን አረዳድ ከፍ ማድረግ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች ጠንካራ የሆነ ባህላዊ መሠረት ባላቸው የኦርቶዶክስ ማኅበረሰቦች ውስጥ ከሴቶች እና ትዳር ጋር ተያይዞ ያለውን መጥፎ ልማድ ለመቅረፍ ወሳኝ መሆኑን፡፡

Guidelines for an Orthodox Marriage: St John Chrysostom’s commentaries on man-woman relations, marriage and conjugal abuse

Dr Romina Istratii

March 2021

This paper is dedicated to St John Chrysostom’s commentaries regarding man-woman relations in marriage and the conjugal relationship as they emerge from seven homilies. An attempt is made to provide a reading of these homilies through the Orthodox phronema understood here as the experience-based historical conscience of the Church. The aim is to bring the works of the Church Fathers closer to the current conditions of the Orthodox faithful and improve their awareness of the Orthodox faith. It is our belief that Chrysostom’s commentaries in particular can become an important resource for the alleviation of pernicious attitudes regarding women and marriage associated with tradition-oriented Orthodox communities.